ከአንደበታችን የሚወጡ ቃላቶች በሰዎች ህይወት ላይ ትልቅ ተጸኖ የማሳደር ሀይል አላቸው፡ ቃላት ከአፍዎ ከመውጣቱ በፊት ስለሚናገሩት ነገር ያስቡ !

አንድ የእንቁራሪቶች ቡድን በጫካው ውስጥ እየተጓዘ ከግሩፑ ውስጥ ሁለቱ ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ወደቁ ። ሌሎቹ እንቁራሪቶች በጉድጓዱ ዙሪያ ተሰብስበው ምን ያህል ጥልቀት እንዳለው ባዩ ጊዜ ለሁለቱ እንቁራሪቶች የመውጣት ተስፋ እንደሌለ ነገሯቸው ።
 ሆኖም ሁለቱ እንቁራሪቶች ሌሎቹ የሚናገሩትን ችላ በማለት ከጉድጓዱ ውስጥ ዘለው ለመውጣት ሞከሩ። ምንም እንኳ ሁለቱ እንቁራሪቶች ከጉድጓዱ ዘለው ለመውጣት ቢሞክሩም ከጉድጓዱ አናት ላይ ያሉት እንቁራሪቶች በጭራሽ መውጣት እንደማይችሉ እና ተስፋ እንደሌላቸው ይነግሯቸው ነበር፡፡በመጨረሻም ፣ አንዱ እንቁራሪት ሌሎቹ የሚናገሩትን በመስማት ከጉድጓድ የመውጣት ሙከራውን ተወው እና ሞተ፡፡ ሌላኛው እንቁራሪት የቻለውን ያህል መዝለሉን ቀጠለ ፡፡እንደገናም ከላይ ያልሉት እንቁራሪቶች ሙከራው ተስፋ ቢስ እንደሆነ እና ዝምብሎ መሞት እንዳለበት ነገሩት ። ነገር ግን የበለጠ ጠንከር ብሎ ዘሎ በመጨረሻ ወጣ ፡፡እንቁራሪቱ ሲወጣ ሌሎቹ እንቁራሪቶች “አልሰማህንም ነበር?”አሉት ። እንቁራሪቱ መስማት የተሳነው መሆኑን አስረዳቸው ። እነሱ ሲጮሁ “ውጣ፣ ዝለልል፣ አይዞህ፣ ዝለል ሞክር...” እያሉ የሚያበረታቱ መስሎኝ ነበር አላቸው። 
እና ምን ለማለት ነው... 
ከአንደበታችን የሚወጡ ቃላቶች በሰወች ህይወት ላይ ትልቅ ተጸኖ የማሳደር ሀይል አላቸው፡ ቃላት ከአፍዎ ከመውጣቱ በፊት ስለሚናገሩት ነገር ያስቡ ። የሚናገሩት ነገር በሕይወት እና በሞት መካከል ያለ ልዩነት ሊሆን ስለሚችል፡፡
Post a Comment (0)
Previous Post Next Post