በሕይወታችን ውስጥ የምናደርገው ትግል ጥንካሬያችንን ያዳብራል !

አንድ ሰው አንድ ቀን አንድ ትንሽ ቀዳዳ አየ ። በዚያች ትንሽ ቀዳዳ ሰውነቱን በኃይል ለማስወጣት ሲታገል የነበረ ቢራቢሮ ለብዙ ሰዓታት ቁጭ ብሎ ተመለከተ ።ማንኛውንም ሙከራ እና ጥረት ማድረጉን እስኪያቆም እና በቀዳዳው ውስጥ የተለጠፈ እስኪመስል ድረስ ተመለከተው ፡፡ እናም ሰውየው ቢራቢሮውን ለመርዳት ወሰነ ፡፡አንድ መቀስ ወስዶ ቀዳዳው ውስጥ ቀርቅሮ የያዘውን የክንፍ ጫፍ ቆረጠለት፡፡ቢራቢሮው ያበጠ ሰውነት እና የተቆራረጠ እና የታጠፈ ክንፎች ይዞ በቀላሉ ከቀዳዳው ለመውጣት ቻለ። ሰውየውም ቢራቢሮው ክንፎቹ እስኪጠነክሩለት እና መብረር እስከሚችል ድረስ ይንከባከበው ጀመር። ነገርግን ያ አልሆነም ። ቢራቢሮው በትናንሽ ክንፎች እና በአበጠ ሰውነት በእግሩ እየተብረከረከ መዞር እንጂ መላ ህይወቱን መብረር አልቻለም ፡፡ሰውየው ደግ ልብ ቢኖረውም ቢራቢሮው በቀዳዳው ውስጥ የሚያደርገው ትግል ለቢራቢሮው ህይወት አስፈላጊ መሆኑ አልገባውም ። ቢራቢሮው ከመፈልፈያ ከወጣ በኋላ ለመብረር የሚያስችለውን ትግል ማድረግ ነበረበት ። ቢራቢሮው ለበረራ ራሱን ለማዘጋጀት ከቢራቢሮው አካል ፈሳሽ መውጣት ወደ ክንፎቹ ማስገባት እና ክንፎቹን ማጠንከር ይኖርበታል፡፡
እና ምን ለማለት ነው...
በሕይወታችን ውስጥ የምናደርገው ትግል ጥንካሬያችንን ያዳብራል ። ያለ ትግል በጭራሽ አናድግም ፤ በጭራሽ አንጠነክርም። ስለሆነም ተግዳሮቶችን በራሳችን መፍታት እጅግ አስፈላጊ ነው። እንዳንድ ጊዜ የሌሎች እርዳታ ለአደጋ ያጋልጣል፡፡



Post a Comment (0)
Previous Post Next Post