የቀድሞ የዩኒቨርሲቲ ተማሪወች የቀድሞ መምህራቸውን ለመጎብኘት በመህራቸው ቤት ተሰበሰቡ። በመካከላቸው ውይይቱ ጦፈ። በመካከላቸው የነበረው ውይይት ብዙም ሳይቆይ ስለ አስጨናቂ ሥራቸው እና ስለ ህይወታቸው ተለወጠ። መምህሩ ወደ ኩሽናቸው ሄዶ አንድ ትልቅ የቡና ፔርሙስ እና የተለያዩ የቡና ስኒወችን ይዞ ተመለሰ፤ ከእነዚህም መካከል የፕላስቲክ፣ የብርጭቆ፣ የሸክላ ስኒወች ይገኙበታል።
መምህሩ ቡና ከቀዳ በኋላ ስኒ እንዲያነሱ
ጠየቃቸው።
ሁሉም ተማሪዎች ቡና በእጃቸው ከያዙ በኋላ መምህሩ “ሁሉም የሚያማምሩ ስኒወች ተወስደው
በጣም ርካሹ ብቻ እንደቀሩ አስተውላችኋል? ብሎ ጠየቃቸው። “ከውጭ ሲታይ የሚያማምሩ እና የሚያብለጨልቹ ነገሮችን መሻት በህይወታችን ውስጥ የጭንቀት
እና የችግሮች ምንጭ ነው። የስኒው ማማር ራሱ የቡናውን ጠም አያሳድግም። እንዳውም በጣም ወድ ከመሆኑ የተነሳ ጣእሙን ይደብቃል”
መምህሩ
ቀጠለ....
“ሁሉም ሰው የፈለገው ቡና እንጂ ስኒ አይደለም፣
ነገር ግን ሁሉም ሰው አውቆ ቆንጆ ቆንጆ ስኒወችን ወስዶ
የሌላውን ስኒ ይመለከት
ጀመር።”
“ህይወት ቡና እንደሆነች እናስብ፣ እና ስራ፣ ቤቶች፣ መኪናዎች፣ ገንዘብ እና የስራ መደቦች ስኒወች ናቸው። ያለን የስኒ አይነት
የሕይወታችንን ጥራት አይገልጽም ወይም አይለውጥም ”
እና ምን ለማለት ነው?
አንዳንድ ጊዜ ቡና በያዘው ጽዋ (ስኒ) ላይ
ብቻ በማተኮር መደሰት አንችልም። ደስተኛ መሆን ማለት በዙሪያዎ ያሉት ነገሮች ሁሉ ፍጹም ናቸው ማለት አይደለም። ሰላም እና መረጋጋት በህይወታችን ለማግኘየት ከጉድለቶች
እና እንከኖች ባሻገር ማየት እንዳለብን ልኖስን ይገባል። ሰላም በአንተ ውስጥ እንጂ በሙያህ፣ በስራህ፣ በምትነዳው መኪና ወይም
ባለህ ቤት ውስጥ አይኖርም።