አንድ መርከብ ሞተሩ ተበላሽቶ ስራ አቁሞ ነበር።
የመርከቡ ባለቤቶች እና ሰራተኞቹ ብዙ መሐንዲሶችን አስፈተሹ። መሀንዲሶቹም ብዙ ግዙፍ ከባድ ዕቃዎችን ተጠቅመው መጠገን ባለመቻላቸው ሞተሩ ከባድ ውድቀት የደረሰበት በመሆኑ መጠገን እንደማይቻል ተስማሙ። ሌላ የመሐንዲስ ቡድን እንዲጠግነው አመጡ። ነገር ግን ምንም ውጤት አላስገኘም።
በዚህ አይነት ሁኔታ ባለ ውጥረት ፣ በመርከቡ ውስጥ ካሉት ሰራተኞች አንዱ የምህንድስና ዲግሪ እና የምስክር ወረቀት የሌላቸው አዛውንት መካኒክ ነበሩ። ሽማግሌው መካኒክ የመርከቡን ችግር እንዲፈታ ሀሳብ ቀረበላቸው።።
ሽማግሌው መጣ። በአንድ እጁ በጣም ትንሽ ቦርሳ ይዞ ነበር። ሽማግሌው ለአንድ ሰአት ያህል ሞተሩን ከላይ እስከታች እያየ እና እየፈተሸ ቆየ። በመጨረሻም ከውስጡ ትንሽ መዶሻ በስተቀር ምንም ያልያዘውን ቦርሳውን ከፈተ።
መሀንዲሶቹ ያ ሽማግሌ ምን እንደሚያደርግ በጉጉት እየጠበቁ ነበር። እናም ሽማግሌው መዶሻውን ያዘና በእጁ የተወሰነውን የሞተር ክፍል መታ መታ በማድረግ ሞተሩን አስተካለው። መርከቧ በጥሩ ሁኔታ ላይ ሆነች ።
ከባባድ እና ውስብስብ መሰራሪያወችን ተጠቅመው መጠገን የተሳናቸው መሀንዲሶች እና የሰርቲፊኬት ባለቤቶች ፣ አዛውንቱ እጅግ በጣም ጥንታዊ በሆነ መሳሪያ ይህን ባደረገ ጊዜ ወደ እርሱ ተመለከቱት እና ተገረሙ።
የሒሳቡም ጊዜ ደረሰ ። ሰውዬው አሥር ሺሕ ጠየቃቸው ። በጣም የሚያስደንቀው ደግሞ የጠየቀው ዋጋ ነው!
“ምን ሰለሰራህ ነው 10ሽ ምንከፍልህ ?” ብለው ጠየቁት።
ሽማግሌውም “ከጠየቁት ዋጋ መጠን የሚበልጥ ሞተር ጠግኛለሁ።” አላቸው።
እናም መሀንዲሶቹ ለሽማግሌው ደረሰኝ እንዲዘጋኝ ተስማምተው ፣ ደረሰኙ ላይ ምን ምን ወጪ ተደርጓል ብለን እናካት? አሉት
ሽማግሌው መለሰ “እሺ” አለ። እስክሪብቶና ወረቀት ይዞ የሚከተለውን ጻፈ:-
"ለተጠቀምኩት መዶሻ 15 ፣ እና 9985 የት ቦታ በመዶሻ መመታት እንዳለበት በትክክል ስለለየሁ”
እና ምን ለማለት ነው ?
ጥረት ማድረግ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን ልዩነቱ ያለው ጥረቱን የት እና በምን አይነት
ሁኔታ መፈጸሙ ላይ ነው።