አንድ ሰው ኢብራሂም ቢን አድሀምን አነጋገረው።
ሰውየው፡- በዚች አለም በረከት የሚባል ነገር የለም!!!
ኢብራሂም ቢን አድሃም እንዲህ ሲል መለሰ፡- ውሻና በጎች አይተሃል?
ሰውየው፡- አዎ !
ኢብራሂም ፡- የትኛው ነው የበለጠ የሚወልደው?
ሰውየውም፡- ውሾች ሰባት ይወልዳሉ፣ በጎቹ ግን ቢበዛ ሦስት !
ኢብራሂም፦ ዙሪያውን ብትመለከት የትኛው የበለጠ ቁጥር ያለው?
ሰውየው፦ በጎች ይበዛሉ።
ኢብራሂም ፡- በቁጥር የሚበልጡት የሚታረዱት አይደሉምን?
ሰውየው፡- አዎ !
ኢብራሂም ፦ እንዴት ያለ መታደል ነው!!!
ሰውየው ፦ እና ለምን ያ ሆነ?! (በጎች ከ ውሾች በበለጠ በረከት ለምን አገኙ?)
ኢብራሂም ፦ ምክንያቱም በጎቹ ሌሊት ሌሊት ተኝተው ጎህ ሳይቀድ ነቅተው ስለሚነሱ የምሕረት ጊዜን ስለሚገነዘቡ በረከት ይወርድላቸዋል። ውሾች ግን ሌሊቱን ሙሉ ይጮኻሉ፣ ጎህ ሲቀድም ስለሚያንቀላፉ፣ ቀን ቀን ይተኛሉ፣ የምሕረትም ጊዜም ያልፋቸዋል።
በምሽት መጠጥ ቤቶች ፣ በዳንኪራ እና ጭፈራ ቤቶች ጊዜያቸውን
የሚያሳልፉ ፣ በራሳቸው፣በገንዘባቸው እና በቤተሰቦቻቸው ላይ
በረከቱን ያጡት እነሱ ናቸው ። እራሳችንን እናስብ እና እንከልስ ።