ሹክሹክታውን መስማት ወይም ድንጋይ እስኪጥልብን መጠበቅ የእኛ ምርጫ ነው !

እንድ ነጋዴ በፍጥነት እየነዳ ሳለ የመኪናው በር በድንጋይ ተመታ እና በቅጽበት ፍሬን ይዞ ተብሳጭቶ እየተሳደበ ከሚኪናው ወረደ።

የተናደደው ሰው ከመኪናው ዘሎ ወጣና በአቅራቢያው ያገኘውን ልጅ እጁን ያዘና “ምነው ምን ነካህ የመኪናየ በር በድንጋይ የመታሀው” ብሎ ጮህበት። “ለምን እንዲህ አደረግክ?” ልጁ በጣም ፈርቶ ነበር ነገር ግን በጣም ጨዋ ልጅ ነበር። እና ይቅርታ ጠየቀ። “ይቅርታ ጌታዬ። ሌላ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም ነበር” አለ። "ድንጋይ መወርወር ነበረብኝ ምክንያቱም እርዳታ ለማግኘት ማንም ሰው አላቆመለኝም።" አለ ልጁ እንባው በጉንጮቹ  እየወረደ። ወደቆመ ዊልቼር እና ከዊልቸሩ ወድቆ ወደፊት ተንከባሎ በወደቀ ልጅ ላይ እየጠቆመ።“ይህ ወንድሜ ነው፣ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል። እሱን ማንሳት አልቻልኩም።

ልጁ እንዲህ አለ “በተሽከርካሪ ወንበሩ እንድመልሰው ልትረዳኝ ትችላለህ? ተጎድቷል እና ለእኔ በጣም ስለከበደኝ ነው። በፍጥነት የወደቀውን ልጅ ከወደቀበት አንስተው ተሽከርካሪ ወንበሩ ላይ አስቀመጡት። ቁስሉንም በጨርቅ ሸፋፈኑለት ።

ሾፌሩ ሁሉም ነገር መልካም እንደሚሆን ሲያስብ ወደ መኪናው ተመለሰ። “እጅግ አመሰግናለሁ፣  ፈጣሪ ይባርክህ” አለ አመስጋኙ ልጅ። ነጋዴው ከመኪናው ሲወርድ ተበሳጭቶ በተናገራቸው ቃላቶች ተጸጸተ። ከመኪናው ሲወርድ በድንጋይ የተሰረጎደውን የመኪናውን በር እያተመለከት ነበር። በመኪናው ላይ የደረሰው ጉዳት በጣም ጎልቶ የሚታይ ነበር። ነገር ግን ነጋዴው ልጁን ረድቶ ወደ መኪናው ከተመለሰ በኋላ  አንድ መልክት ወደ ሀሳቡ መጣለት ፦ " በህይወትህ አንድ ሰው ትኩረትህን ለመሳብ ድንጋይ እስኪወረውርብህ ድረስ አጠብቅ"

እና ምን ለማለት ነው?

ሕይወት በነፍሳችን ውስጥ ያንሾካሹካል፣ ከልባችን ጋር ይነጋገራል። አንዳንድ ጊዜ እኛ ሳንሰማው ስንቀር ድንጋይ ይጥልብናል። ሹክሹክታውን መስማት ወይም ድንጋይ እስኪጥልብን መጠበቅ የእኛ ምርጫ ነው ።

Post a Comment (0)
Previous Post Next Post