የብዙ ዓመታት ልምድ ያለው አናጺ ጡረታ ለምወጣት እየተዘጋጀ ነበር። ከባለቤቱ እና ከቤተሰቡ ጋር የተደላደለ የጡረታ ህይወት ለመኖር ስራውን ለቆ ለመውጣት ማቀዱን ለአሰሪው አስታውቀ። አሰሪው ጥሩ ልምድ ያለው አናፂ ስራውን ለቆ ለመውጣት በማቀዱ ትንሽ አበሳጭቶታል።ነገር ግን ስራውን ለቆ ከመውጣቱ በፊት ሌላ አንድ ምርጥ ቤት እንዲሰራለት አናጺውን ጠየቀ።
አናጺው
ከአሰሪው ጋር ተስማማ። ነገር ግን ልቡ እንደ ቀድሞው በስራው ውስጥ አልነበረም። ዝቅተኛ ቁሳቁሶችን ተጠቅሞ ፣ በፍጥነት እና
በግዴለሽነት ቤቱን ሰርቶ አስረከበ። አናጺው ቤቱን ሲጨርስ አሰሪው ቤቱን ሊፈትሽ መጣ።
ቤቱን
ዞር ዞር ብሎ ተመለከተ እና ቤቱን ለቆ ከመውጣቱ በፊት ቁልፉን ለአናጺው ሰጠው። እንዲህ
አለው “ይህ የእርስዎ
ቤት ነው፣ በጡረታ ዘምንህ ከቤተሰቦችህ ጋር እንድትኖርበት ለአንተ የማቀርብልህ ልዩ ስጦታ” አለው። ምንም እንኳን በጣም የሚያስደንቅ ቢሆንም በውስጡ ጥልቅ ሀፍረት ተሰማው። የራሱን
ቤት እየሠራ መሆኑን ቢያውቅ ኖሮ ሁሉንም ነገር በተለየ መንገድ ያደርግ ነበር። አሁን በደንብ ባልተገነባ ቤት ውስጥ ሊኖር ነው።
እና ምን ለማለት ነው?
ሁላችንም የህይወታችን አናጺ ነን። እንዳለመታደል ሆኖ ህይወታችንን በተዘናጋ መንገድ እንገነባለን ፣ከድርጊት ይልቅ ምላሽ በመስጠት፣ከተሻለ ይልቅ
ባነሰ መንገድ ለመሰለፍ እና ለማለፍ እንመርጣለን። ለህይወትህ ምርጡን ስጥ። አስተሳሰብህ
እና ዛሬ የምትመርጠው ምርጫ ነገ ህይወትህ ይሆናል እና ዛሬን በጥንቃቄ ገንባ።