በሞት ፊት ድኻና ባለጸጋ ፤ ጐበዝና ፈሪ ፤ ትልቅና ትንሽ ፤ ዐዋቂና ደንቆሮ ሁሉም ትክክል ናቸው ። ሁሉም ደግሞ ሞትን መፍራት አለባቸው !

አንድ  ዐዋቂ  ሰውና  አንድ  ማይም በጀልባ  ሲሄዱ  ትልቅ  ነፋስ  ተነሥቶ  ጀልባውን  ሊገልብጠው  በወዲያና  በወዲህ  እያንገላታው  በጣም  የሚያስፈራ  ሆነ ዐዋቂው ሰው  በዚህ  ጊዜ  እጅግ  ፈርቶ  ተንቀጠቀጠ ማይሙ ግን  ምንም  ሳይፈራ  ጀልባው  እንዳይገለበጥባቸው  ከማዕበሉ  ጋራ  እየታገለ  ከብዙ ጭንቅ  በኋላ  በደኅና  ከጠረፍ  ደረሱ።
ማይሙ በጣም  እየሣቀ  አዬ  የኛ ሊቅ  እኔ  ደንቆሮ  የተባልሑት  ሰው  ምንም  ሳልፈራ  አንተ  ተምረሀል፤ ብዙ ነገር  ታውቃለህ  የተባልኸው  ሰው  ይህን  ያህል  በፍርሀት  ስትንቀጠቀጥ  በማየቴ  እጅግ  አድርጎ  ያሥቀኛል  እያለ  ቢያሾፍበት፤ ዐዋቂው  ተናዶ አንተ  ያልፈራህበት  ምክንያት ብትኖርም ፤ብትሞትም  ለዓለም  ምንም  የማታጐድል  መሆን ህን  ስለምታውቀው  ነው  እኔ  ግን  ብሞት  ለዓለም  ብዙ እንደማጐድል  ዐውቃለሁና  ሞትን  በጣም  አድርጌ  መፍ ራቴ  ስለዚህ  ነው  አለው
የተማሩ  ሰዎች  ምን  ጊዜም  ቢሆን  የሚመልሱት  መልስ  አያጡም  ለማለት  ነው  እንጂ ይህን  የጻፍንላችሁ  ይህ  ዐዋቂ  ማይሙ  ስለሣቀበት  በንዴት  የተናገረው ይህ  ቃል  የተገባ  ነው ለማለት  አይደለም
በሞት  ፊት  ድኻና  ባለጸጋ ጐበዝና  ፈሪ ትልቅና  ትንሽ ዐዋቂና  ደንቆሮ  ሁሉም  ትክክል  ናቸው ሁሉም  ደግሞ  ሞትን  መፍራት  አለባቸው

ከበደ ሚካኤል እንደጻፈው 

Post a Comment (0)
Previous Post Next Post