ሰነፎች ቅሬታ ሲያሰሙ ብልሆችግን በደግነት ፣ በልግስና እና ነገሮችን ለማከናወን ፈቃደኛ በሆነ ልባቸው በህይወታቸው ውስጥ እድልን መፍጠር ይችላሉ !

 በጥንት ዘመን አንድ ንጉስ በመንገድ ላይ አንድ ቋጥኝ ያስቀምጥና ራሱን ደብቆ ድንጋዩን ከመንገዱ የሚያነሳ ካለ ለማየት ይከታተል ነበር ። አንዳንድ ሀብታሞች፣ ነጋዴዎች እና የቤተመንግሥት ሰዎች በድንጋዩ አጠገብ ተመላለሱ ። ሰዎቹ መንገዶቹን ንጹህ ባለማድረጋቸው፣ ንጉሱን ከመወቀስ ውጭ አንዳቸውም ድንጋዩን ከመንገዱ ለማስወገድ ጥረት አላደረጉም። ከዚያ አንድ ገበሬ አትክልት ተሸክሞ መጣ ። ገበሬው ወደ ድንጋዩ ሲቀርብ ሸክሙን ተሸክሞ ድንጋዩን ከመንገዱ ለመግፋት ሞከረ። ከብዙ ግፊት እና ውጥረት በኋላ በመጨረሻ ተሳካለት።ድንጋዩን ከመንገድ አስወገደው። ገበሬው አትክልቱን ሽጦ ወደቤቱ ሲመለስ ድንጋዩ በነበረበት መንገድ ላይ አንድ ቀረጢት ተቅምጦ ተመለከተ ። በቀረጢቱ ውስጥ ብዙ የወርቅ ሳንቲሞችን እና ከንጉሱ የተላከ ማስታወሻ አገኘ። ማስታወሻው ድንጋዩን ላስወገደው ሰው እንደሆነ ያስረዳል ። 
እና ምን ለማለት ነው...
በህይወት ውስጥ የሚያጋጥሙን መሰናክሎች ሁሉ እኛነታችንን ለማሻሻል እድል ይሰጡናል ። ሰነፎች ቅሬታ ሲያሰሙ ብልሆችግን በደግነት ፣ በልግስና እና ነገሮችን ለማከናወን ፈቃደኛ በሆነ ልባቸው በህይወታቸው ውስጥ እድልን መፍጠር ይችላሉ። 
Post a Comment (0)
Previous Post Next Post