እኛ ኢትዮጵያውያን ባሁኑ ግዜ አንድ በግድ ልንከተልውና ልንፈጽመሙ የሚገባን ሀሳብ ከዚህ ቀጥሎ ያለው ነው ።

ከበደ ሚካኤል እንደጻፈው 

አንደኛ ፡  ኢትዮጵያዊ  የሆንህ  ሰው ፡ ሁሉ ፡ ሰንደቅ ፡ ዓላማህ ፡ አገርህና ፡ ነጻነትህ ፣ የሚጠቁበትን ፡ ነገር ፡ ለማስወገድ  መይም ፡ ደግሞ ፡ እነሱ የሚጠቀሙበትን ሥራ  ለመፈጸም ፡ ብለህ ፤ በሞትህ ጊዜ  በሰማይና  በምድር ስምህ በወርቅ ፡ ቀለም  የሚጻፍበትን  የሰማዕትነት ፡ ሥራ በመሥራትህን ፡ ልብህ ፡ ተረድቶት ፡ ደስ  ይበለው።

ሁለተኛ ፡  አገርን  መመውደድ ፡ ማለት ፡ አገርህ ፡ የምትጠቀምበትንና የምትከበርበትን ሥራ  መሥራት  ነው ።

ሦስተኛ፡አገርህንና  ወገንህን ፡ የሚያስንቅ ፡ መይም ፡ የሚጎጻ ፡ ሥራ ፡ ከመሥራት ፡ መሞት ፡ ይሻልሃል ።

አራተኛ ፡  እኛ ፡ ኢትዮጵያውያን የምንሰራው ሥራ መልካም ፡ ቢሆን ፡ ኣግራችን ፡ኢትዮጵያ ፡ እንደምትከበር ፤ የምን ሰራው ሥራ ፡ መጥፎ ፡ ቢሆን  ግን እንደምትዋረድ፡ ኣትርሳ ።
 
አምስተኛ ፡ ኢትዮጵያ አገርህ ፡ ከሌሎቹ ፡ ከማንኛምቹም አገሮች ፡ ሁሉ  ይልቅ  የምትበልጥብህ ፡ መሆንዋ ፡ ቀንም ፡ ሆነ ፡ ሌሊት  በሀሳብህ ፡ ውስጥ ፡ ሳይረሳና ሳይዘነጋ ፡ ተጽፎ ይኑር ።

ስድስተኛ  ማንኛውም ፡ የውጭ  አገር ፡ ሰው ፡ ለተወለደባት። አገሩ ፡ የሚያስብላት ፡ መልካም ፡ ሀሳብ  ወይም  የሠራላት፡ መልካም ፡ ሥራ ፡ ሲናገር በሰማህ ወይም ፡ ተጽፎ፡ ባየህ ፡ ጊዜ  ኣንተም  ደግሞ  እንደዚሁ ይህንኑ ያህል ፡ ላገርህ ለኢትዮጵያ ልታስብላትና ፡ ልትሠራላት  የሚግባህ መሆኑን ዕወቀሙ ።

ሰባተኛ፡ አንድ ኢትዮጵያዊ  ሲበደልና ፡ ሲጠቃ  ባየህ  ጊዜ የተበደለችውና ፡ የተጠቃችው  እናትህ  ኢትዮጵያ መሆኗን ተረዳው።

ስምንት፡ ኢትዮጵያ  አገርህ በእውነት ትልቅ  ሳትሆንና  ወንድሞችህ ኢትዮጵያውያን ፡ ሁሉ ሳይደላችው ላንት ብቻህን ፡ የምታግኘሙ ደስታ  ገንዘብና ፡ ተድላ በሕልም እንደተገኘ ፡ ወርቅ እና መና  ባዶ ሆኖ  የሚቀር ፡ መሆኑን ፡ ልብህ ፡ አይዘንጋው ።

ዘጠነኛ፡ ብዙ ገንዘብና ብዙ ርስት ፡ ካገኘ ይልቅ ለአገሩ ፡ ትልቅ ፡ ሥራ ፡ የሠራ ፡ ሰው ፡ ስሙ ፡ ለዘለዓለም  ታሪክ ፡ ሲጠራ ፡ ይኖራል ።

አስረኛ፡ ሌሎች ፡ የዓለም ፡ ነገሥታት ፡ ከደረሱበት ፡ የስልጠኔ ፡ ደረጃ ፡ ላይ ፡ አገራችን ፡ ኢትዮጵያ ፡ በቶሎ እንድትደርስ እኛ ፡ ኢትዮጵያውያን ፡ ሁሉ ፡ ማሰብና ፡ መጣጣር ፡ ይገባናል ። ድካማችንና ፡ ትጋታችንም ፡ በተለየ ፡ ለዚሁ ፡ ሀሳብ ፡ ብቻ ፡ እንዲሆን ፡ ያስፈልጋል ።

አስራ አንደኛ፡ በአንድ ፡ ዓመት ፡ ውስጥ ሥስት ፡ መቶ ፡ ስድሳ ፡ አምስት ፡ ቀኖች ፡ አሉ ። በአራት ዓመት ፡ አንድ ዩ ጊዜ ፡ ግን ሦስት፡ መቶ ፡ ስድሳ ፡ ስድስት ፡ ቀኖች ፡ ይሆናሉ ። ይኸውም ፡ የሚሆነው ፡ ጳጉሜ ስድስት ፡ ቀን ፡ በምትውልበት ፡ ዘመን ፡ ነው ።

በአንድ ፡ ዓመት ፡ ውስጥ ፡ አሥራ ፡ ሁለት ፡ ወሮች ፡ አሉ ። እነሱም መስከረም ጥቅምት  ሓዳር  ታኅሳ ሥ  ጥር ፤ የካቲት ፤ መጋቢት  ሚያዝያ ግንቦት ፣ ሰኔ ፤ ሐምሌ ፤ ነሐሴ ናቸው።

በሦስቱ ፡ ዓመት ፡ አምስት  ቀን ፤ በአራተኛው ኣንድ ፡ ጊዜ ፡ ስድስት ፡ ቀን ፡ የምትሆን ፡ ጳጉሜ  አለች ። 

በአንድ ፡ ዓመት  ውስጥ : አምሳ  ሁለት  ሳምንቶች አሉ።  በአንድ ፡ ሳምንት ፡ ውስጥ ሰባት ቀናቶች አሉ ። እነሱም ፦ ሰኞ ፤ ማክሰኞ ፡ ረቡዕ ፤ ኅሙስ፣ አርብ ፣ ቅዳሜ እና እሁድ ናቸው። 

የዓመቱ ወሮች ፡ በአራት : ክፍል ይከፈላሉ ። እነሱም ጥቢ፣ በጋ ፣ በልግ እና ክረምት ናቸው።

*

እግዚአብሄርን መፍራት የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ ነው።

*

ከማዘዝ በፊት አስቀድሞ መታዘዝን ማወቅ ያስፈልጋል።

*

ጥሩም ነገር ቢሆን ከመጠን ካለፈ ሁልጊዜ መጥፎ ነው።

*

ተቢት እና ውርደት አካል እና ጥላ ናቸው ሳይለያዩ ሁልጊዜ ቀዳሚ እና ተከታይ ሁነው ይኖራሉ።

*

እህል እና ውሀ ሰውነትን እንደሚመግቡት ሁሉ መጽሀፍትን ማንበብ እንደዚሁ መንፈስን ይመግባል።

*

ከበላይህ ያሉትን ሰወች እያየህ ልብህ ቅናት አይደርበት ። ይልቅስ ካንተ በታች ያሉትን ችግርተኞች እየተመለከትክ እድልህ ከነሱ የተቻለ በመሆኑ ፈጣሪህን እመስግን።

*

ማንም ሰው ቢሆን መከራ ወድቆበት ባየህ ጊዜ አትፍረድበት ። ወይም አትጨክንበት ።  በእሱ ላይ የደረሰ መከራ ምናልባት ባንተም ላይ ወደፊት ሳይደርስብህ አይቀርም።

*

ምንም እንኳ የሚያስመሰግንህ ትልቅ ስራ ብሰራ ምንጊዜም ቢሆን አትመካበት። ትምክህት ማንኛውንም  ዋጋ ቢሆን ያቀለዋል። ትህትና ኝ ከሁሉ ሙያ የበለጠ ዋጋ ያለው ባህሪ ነው።

*

የፈረንሳዩ ፈላስፋ እንዲህ ይላል፡ ቃል ለሰው ልጅ የተሰጠው ሀሳቡን እንዲገትጽበት ነው ይባላል። ነገር ኝ ሀሰት ነው። ቃል ለሰው ልጅ የተሰጠው በዋናነት ሀሳቡን እንዲሸፍንበት ነው።

*  

ሰው በህይወቱ ሲኖር የሚያገኘው መልካም ነገር ሁሉ የሚቀበለው ከተወለደበት አገር ስለሆነ አስፈላጊ ምክኒያት በመጣ ጊዜ ያለውን መልካም ነገር ሁሉ ህይወቱን እንኳ ሳይቀር ሳያመነታ ላገሩ ሲ፤ል ለሰዋ ይገበዋል።
*  

እንድ ፡ ትልቅ ፡ ሊቁ ፡ ስለ ፡ ስንፍና ፡ መጥፎነት ፡ ሲናገር እንዲህ ፡ አለ “ ማናቸውንም ፡ ዐይነት' ጥፋት ፡ ያጠፋ ፡ ሰው , ሁሉ ፡ ይቅርታ ፡ ሲደረግለት' የተገባ ፡ ነው ። ምሕረት ፡ ሊደረግ ለት፡ የማይግባ ፡ አንድ፡ ብቻ ፡ አለ ፡ እሱም ሰነፍ ሰው ነው።
*

ከጥንት፡ ጀምሮ ፡ ሲነገር ፡ የሚኖር፡አንድ፡ የላቲን ፡ተረት፡ እንዲህ ይላል " ጦርነት እንዳይመጣብህ ፡ ብትፈልግ ሁልጊዜ' ለጦርነት' የተሰናዳህ ፡ ሆነህ ፡ መቀመጥ ይገባሀል ።
*  

በጌታና በድኻ ፡ ሰው ፡ መካከል ' የሚገኘው ልዩነት በጣም ፡ የተራራቀ ፡ ነው ይሁን ፡ እንጂ ፡ ጌትነትና፡ ድኽነት ጐን ለጐን ሲሄዱ ፡ ይኖራሉ ።
*

ጸሀይ ጠዋት ጠዋት የምትወጣው የሱን ድምጽ ሰምታ ' እየመሰለው ፡ በልቡ የሚኮራ አንድ አውራ ዶሮ ነበር ይባላል። በሰወችም መካከል ለሰሩት የማይችሉትን ስራ የሰሩ እየመሰላቸ የሚኩራሩ ፣ ሲመኩ የሚታዩ ሰወች ይገኛሉ።

*  

ምቀኛ ሰው የክፋቱ ብዛት የሞቱ ሰአት በደረሰች ጊዜ እኔ ከሞትኩኝ በኋላ አለም ጨለማ ሁና ትቅር ብሎ በማሰብ የሚቻለው ቦሆን ኖሮ ጸሀይን አጥፍቷት ለመሞት በወደደ ነበር። ቅን ሰው ኝ ለአለም የሚጠቅም ስራ ለመስራት ሲል ህይወቱን ይሰዋል።

*
የሰው ሙያ ሦስት ፡ ዐይነት ፡ ነው ። አንደኛው ፡ ማሰብን ማወቅ ሁለተኛው ፡ መናገርን ፡ ማወቅ ፡ ሦስተኛው መሥራትን ማወቅ ።| አብዛኞቹ ፡ ብልሆች ፡ የሚባሉ ሰዎች ፡ ከእነዚህ ከሦ ስቱ አንደኛውን ' ብቻ : ነው ፡ የሚይዙ። ወይም ፡ መሥራት ፣ ያውቁና ፡ ትክክል ፡ ማሰብ ፡ አይችሉ ፡ ይሆናል ። ስለዚህ ትክክል ካለማሰባቸው ፡ የተነሣ ፡ ደክመው ፡ የሠሩት ፡ ሥራ ፡ ሁሉ ፡ ይፈርሳል ። ወይም ፡ ደግሞ ፡ ንግግር ፡ አሳማሪዎች ፡ ዐሳባቸውና ፡ ሥራቸው ብላሽ ይሆናል ። ትክክል ፡ ዐስቦ : ያሰበውን ትክ ክል ፡ አድርጎ ፡ በቃል ፤ ወይም ፡ በጽሕፈት ፡ አስረድቶ ፡ እንዳሰበውና ፡ እንደተናገረውም ፡ አድርጎ ' ትክክል ፡ የሚሠራ ፡ ሰው ፡ እውነት ፡ ትልቅ ፡ ዐዋቂ ፡ ነው ሊባል ይቻላል ።

*
ዶስታ ፡ ምንድን ፡ ነው'ብለው ፡ ቢጠይቁት ፡ አንዱ ፡ ሊቅ ፡ ደስታ ፡ ማለት ፡ ጤንነት ፡ ነው ፡ ብሎ ፡ ተናገረ። ጤንነትሳ፡ደግሞ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ብለው መልሰው ፡ ቢጠይቁት ፤ ጤንነት፡ ማለት፡ ሁሉም ፡ ነው ፡ ብሎ ፡ መለሰ ። እውነት ፡ ነው ፡ ጤንነት፡ ከሌለ ፡ ሁሉ ፡ ነገር ፡ ከንቱ ፡ ነው ። ጤንነት ፡ ካለ ፡ ግን ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ መገኘቱ ፡ አይቀርም ።

*
በዓለም ፡ ላይ ፡ ትልቅ ፡ ሥራ ፡ ለመሥራት ፡ የሚቻለው ሠሪው ፡ ሰውና ፡ ለመሥራት፡ የተመቸበት ፡ ጊዜ ፡ እነዚህ ሁለቱ : ሲገናኙ ፡ ነው ። ትልቁን ፡ ሥራ ለመሥራት ፡ የሚችለው ፡ ሰው ፡ ባልተመቸ ፡ ጊዜ ፡ ሲፈጠር ሊሠራው ፡ የሚችለውን ፡ ሥራ፡ሳይሠራው ፡ መቅረት ፡ ግድ፡ ይሆንበታል ። ልሥራም ፡ ቢል ጊዜው: አይደለምና ፡ አይሆንለትም ። ትልቅ ፡ ሥራ ለመሥራት፡የተመቸ፡ በሆነበት፡ ጊዜ ፡ ደግሞ ፡ ሊሠራው ፡ የሚችል ፡ ሰው ፡ ባለመፈጠሩ፡ መልካሙ ፡ ጊዜ በከንቱ ፡ ያልፋል ። እነዚህም፡ ሁለቱ፡ተፈላላጊ ነገሮች፡የሚገናኙት በብዙ፡ ዘመን ፡ ውስጥ፡ ጥቂት፡ጊዜ ነው ።



Post a Comment (0)
Previous Post Next Post