አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ልጅ አብረው ይጫወቱ ነበር። ልጁ የሚያማምሩ እብነበረድ ነበሩት ። ልጅቷ ታፋጭ ከረሜላ ነበሯት። ልጁ ለልጅቷ ሁሉንም ጣፋጮች እንድሰጠው እና እሱ ሁሉንም እብነበረድ እንዲሰጣት ጥያቄ አቀረበ። ልጅቷም ተስማማች። ልጁ ሁሉንም እብነ በረድ ለልጅቷ ሰጣት ። ነገር ግን ትልቁን እና በጣም የሚያምር እብነ በረድ በድብቅ አስቀርቶ ነበር። ልጅቷ ቃል በገባችው መሰረት ሁሉንም ጣፋጮቿን ሰጠችው። በዚያ እለት ምሽት ልጅቷ በሰላም ተኛች። ነገር ግን ልጁ ጥሩውን እብነበረድ በደበቀበት መንገድ ልጅቷም አንዳንድ ጣፋጭ ከረሜላውችን እንደደበቀች በማሰብ ልጁ መተኛት አልቻለም።
እና ምን ለማለት ነው?
በሰቶ መቀበል ወቅት የእርስዎ የሆነውን መቶ በመቶ ካልሰጡ፣ ሌላኛው ሰው መቶ በመቶ እንደሰጠ ሁልጊዜ ጥርጣሬ ውስጥ ይገባሉ።