አንድ ጊዜ አንድ ውሻ በመስታወት የተሞላ ሙዚየም ውስጥ ገባ። ሙዚየሙ ልዩ ነበር ፣ ግንቦቹ ፣ ጣሪያው ፣ በሮች እና ወለሎች እንኳን ከመስታወት የተሠሩ ነበሩ ። ውሻው የእሱን ነጸብራቅ አይቶ በሚገርም ሁኔታ በአዳራሹ መካከል ፈዞ ቀረ። ከላይ እስከታች ከየአቅጣጫው ውሾች ከበውት ይመለከት ነበር።
ውሻው ጥርሱን አውጥቶ በተመሳሳይ መንገድ ምላሽ የሰጡትን ሁሉንም ነጸብራቆች ጮኸባቸው። በጣም በመደንገጥ፣
ውሻው በሀይል ጮኸ፣ የውሾቹን ምላሽ ተከትሎ ብዙ ጊዜ ጮኸ። ውሻው የበለጠ ጮኸ። ውሻው በሀይል በሚጮህበት ጊዜ ከጎን ወደ ጎን
ሲንቀሳቀስ ከመስታወቱ ጋ ስለተላተመ የምስታወት ስባሪ ወግቶት ሞተ።
በማግስቱ ጠዋት የሙዚየሙ የጥበቃ ሰራተኛ ምስኪኑን እና ህይወት የሌለውን ውሻ በህይወት አልባ የውሻ ነጸብራቆች ተከቦ አገኘው። ውሻውን የሚጎዳ ምንም ነገር አልነበረም። ውሻው ከራሱ ነጸብራቆች
ጋር ተላትሞ ሞቶ አገኘው።
እና ምን ለማለት ነው...... ?
ዓለም በራሱ ጥሩ ወይም ክፉ ነገር አያመጣም። በዙሪያችን እየሆነ ያለው ሁሉ የሀሳባችን፣
ስሜታችን፣ ፍላጎታችን እና ድርጊታችን ነጸብራቅ ነው። አለም ትልቅ መስታወት ነች። ስለዚህ መልካም እናድርግ!