በህይወትዎ ውድቀት ቢያጋጥመዎ ፣ ሁል ጊዜ እራስዎን ከወደቁበት ማንሳት እና መመለስ እንዳለብዎ ያስታውሱ !

ህፃናት ቀጭኔዎች በጭራሽ ወደ ትምህርት ቤት አይሄዱም። ነገር ግን በሕይወታቸው መጀመሪያ ላይ በጣም ጠቃሚ ትምህርት ይማራሉ። ሁላችንም ልናስታውሰው የሚገባ ትምህርት !

የሕፃን ቀጭኔ መወለድ ምድርን የሚያናውጥ ክስተት ነው። ህጻኑ ቀጭኔ ገና ሲወለድ ከመሬት በላይ ስምንት ጫማ ርቀት ካለው ከእናቱ ማህጸን ይወድቃል።መሬት ላይ ይፈጠፈጣል! ህጻን ቀጭኔ ለመንቀሳቀስ በጣም ደካማ ነው።

እናት ቀጭኔ ሕፃኗን በፍቅር ለማቀፍ አንዴ አንገቷን ዝቅ ታደርጋለች። ከዚያ አንድ የማይታመን ነገር ይከሰታል። ረጅም እግሯን አንስታ እናት ቀጭኔ በወላድ አንጀቷ ሕፃኑን ቀጭኔ በካልቾ ትጠልዘዋለች ።  ህፃኑ ቀጭኔ ተንፈራግጦ  መሬት ላይ ሲተኛ እናቱ እንደገና ትጠልዘዋለች። እናም እንደገና። ሕፃኑ ቀጭኔ አሁንም እየተንቀጠቀጠ እና እየደከመ እግሮቹ እስኪጠነክሩ በእናቱ እግር ይጠለዛል። ከዛም ህጻኑ ቀጭኔ እየተብረከረከ በእግሮቹ መሄድ ይጀምራል።

በዚህ ሁኔታ ህጻን ቀጭኔ ሰውነቱ ጠንክሮ በእግሮቹ መሄድ ይጀምራል።

እናት ቀጭኔ ለምን እንዲህ ታደርጋለች?

አንበሶች እና ነብሮች የቀጭኔ ስጋ እንደሚወዱ ታውቃለች። ስለዚህ ሕፃኑ ቀጭኔ በፍጥነት መቆም ካልተማረ በሕይወት የመትረፍ እድል አይኖረውም።

ምን ለማለት ነው?

ምንም ያህል ከባድ አወዳደቅ ቢወድቁ አይጨነቁ። ሁል ጊዜ እራስዎን ከወደቁበት ማንሳት እና መመለስ እንዳለብዎ ያስታውሱ።

አብዛኛዎቻችን እንደ ሕፃን ቀጭኔዎች በጣም እድለኞች አይደለንም።  በወደቅን ቁጥር እንድንነሳ ማንም አያስተምረንም። ስንወድቅ፣ ስንዋረድ ዝም ብለን ተስፋ እናደርጋለ እንጂ በሕይወት ለመትረፍ እና ስኬታማ ለመሆን ወደ ነበርንበት ለመመለስን መማር እንዳለብን ለማስታወስ ማንም ሰው ከምቾት ቀጠናችን አያስወጣንም።

የተሳካላቸውን ሰዎች ህይወት ካጠናን ግን አንድ የሆነ ፓተርን እናስተውላለን። ባደረጉት ነገር ሁሉ ሁልጊዜ ስኬታማ ነበሩ? አይደሉም! ስኬት በፍጥነት እና በቀላሉ መጣላቸው? አልመጣላቸውም! በሕይወታቸው ውስጥ ያለ የጋራ ነገር ቢኖር በወደቁ ቁጥር ተመልሶ የመቆም ችሎታቸው (resilience) እንደሆነ እንገነዘባለን።።

የሕፃኑ ቀጭኔ ችሎታ  ግን ይገርማል!

Post a Comment (0)
Previous Post Next Post