ከሳጥኑ ውጭ አስብ !

ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት በአንዲት ትንሽ የጣሊያን ከተማ ውስጥ ትልቅ ዕዳ ያለበት አንድ ነጋዴ ይኖር ነበር። መልከ መልካም ያልነበረ አንድ ባለባንክ ሽማግሌ የነጋዴውን ትንሽ  ሴት ልጅ ይፈልግ ነበር።

ባለ ባንኩ የነጋዴውን እዳ እንዲሰረዝለት ከነጋዴው ጋር ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ፈለገ።  ነጋዴው ከዕዳ ነፃ እንዲሆን ሴት ልጁን ለባለባንኩ እንዲድርለት ፈልጎ ነበር። 

ነጋዴው ይህንን ስምምነት ለመቀበል አልፈለገም። ነገር ግን እዳው በጣም ከመጠን በላይ ስለነበረ ሌላ ምርጫ አልነበረውም።

ባለባንኩ ሁለት ትናንሽ ድንጋዮችን ወደ ቦርሳ እንደሚያስገባ ነገረው። አንደኛው ነጭ እና አንድ ጥቁር ድንጋይ።

ከዚያም ሴት ልጁ ከቦርሳው ውስጥ በጭፍን ድንጋይ መምረጥ ይኖርባታል። ጥቁሩን ድንጋይ ከመረጠች የነጋዴው ዕዳ ይወገዳል እና ልጅቷ የባንክ ሰራተኛውን ማግባት አለባት። ነገር ግን ነጩን ድንጋይ ከመረጠች እዳው ይሰረዛል እና ሴቷ ልጅ ባለባንኩን ሽማግሌ አትዳርም።.

ባለባንኩ፣ የነጋዴው ሴት ልጅ እየተመለከተችው መሆኑን ሳያውቅ ድንጋይ በተሞላው በባንኩ ግቢ ውስጥ መንገድ ላይ ሁለት ጥቁር ድንግዮችን አንስቶ ቦርሳው ውስጥ ጨመረ። እሷም ሁለት ጥቁር ድንጋዮችን አንስቶ ቦርሳው ውስጥ እንዳስቀመጣቸው አስተዋለች። ልጅቷ ከቦርሳው ውስጥ ድንጋይ የምታወጣበት ጊዜ ደረሰ። ልጅቷ 3 ምርጫ ነበራት፦ 

1.     ሙሉበሙሉ አለመምረጥ እና እምቢ ማለት.

2.     ሁለቱንም ድንጋዮች አውጥታ  የባለባንኩን አጭበርባሪነት ማጋለጥ 

3.     ጥቁር እንደሚሆን አውቃ ራሷን ሰውታ አባቷን ከእዳ ነጻ ማድረግ 

ከቦርሳው ውስጥ ድንጋይ አነሳች።  ወዲያው ሁሉም በቆሙበት ድንጋዩን  ጣለችው።

ለባንክ ሰራተኛው እንዲህ አለች - “ይቅርታ፣ እኔ የመረጥኩትን ድንጋይ ለማወቅ እንዲችሉ አሁን ምን አይነት ቀለም ድንጋይ ቦርሳው ውስጥ እንደቀረ ለማየት ቦርሳውን ይመልከቱ።

እርግጥ ነው የቀረው ድንጋይ ጥቁር ነበር። ባለባንኩ ተንኮሉ እንዲገለጥ ስላልፈለገ የነጋዴው ሴት ልጅ የጣለችው ድንጋይ ነጭ መሆን እንዳለበት በመናገር ነገሩን በማስቀየስ ጨዋታውን ቀጠለ። ባለባንኩ የነጋዴውን ዕዳ ሰረዘ።ልጅቷም ቀሪ ሕይወቷን ከባለባንኩ ሽማግሌ ጋር ከማሳለፍ ነፃ ሆነች።

እና ምን ለማለት ነው .... 

አንዳንድ ጊዜ ነገሮችን በተለየ አንግል ማየት ሊኖርብን ይችላል። ሁልጊዜ ለቀረቡት አማራጮች መልስ በመስጠት ችግሮችን መፍታት አይቻልም። ያለውን ሁኔታ ፈትን። በፈጠራ አስብ። በሚቻልበት ጊዜ ፍሬያማ አለምስማማት (productive nonconformity) ውስጥ ተሳተፍ። እውነት እንዲሆኑ የምጠብቀውን ነገሮች ለመጠየቅ አትፍራ። ተግዳሮቶችን ለማሸነፍ ከዚህ በፊት ሰወች ባልሞከሩት መንገድ ማሰብ ይኖርብሀል።

 


Post a Comment (0)
Previous Post Next Post