በአንድ ወቅት አንዲት የሥነ ልቦና ፕሮፌሰር ስለ stress management system ለተማሪዎች ገለጻ እያደረገች ሳለ አንድ ብርጭቆ ውሃ ስታነሳ፣ ተማሪውች የተለመደውን “ይህ ብርጭቆ ግማሽ ባዶ ወይስ ግማሽ ሙሉ?” የሚል አሰልቺ የሳይኮሎጂ ጥያቄ ትጠይቃለች ብለው ጠብቀው ነበር። ይልቁንም፣ “ይህ የያዝኩት ብርጭቆ ውሃ ምን ያህል ከባድ ነው?’ ብላ በፈገግታ ጠየቀች ።
ተማሪዎች ከስምንት አውንስ እስከ ጥንድ ፓውንድ ክብደት ሊኖረው እንደሚችል ገመቱ።
እሷም እንዲህ ስትል መለሰች፡- ‘ከእኔ እይታ አንጻር የዚህ ብርጭቆ ውሀ ክብደት ምንም ለውጥ አያመጣም። የዚህ ብርጭቆ ክብደት እኔ ለምን ያህል ጊዜ እንደያዝኩ ይወሰናል። ለአንድ ወይም ለሁለት ደቂቃ ከያዝኩት፣ በትክክል ቀላል ነው። ለአንድ ሰዓት ያህል ቀጥ ብዬ ከያዝኩት፣ ክብደቱ እጄን ትንሽ ሊያሳምም ይችላል። ለአንድ ቀን ቀጥ ብዬ ከያዝኩት፣ እጄ ሊጨማደድ እና ሙሉ በሙሉ የመደንዘዝ ስሜት ስለሚሰማኝ ብርጭቆውን ወደ ወለሉ እንዳወርድ ያስገድደኛል። ለሁለት ድቂቃም ሆነ ለሁለት ሰአት ብይዘው የብርጭቆው ክብደት ያው ነው። ነገር ግን ረዘም ላለ ጊዜ ስይዘው ለእኔ የሚሰማኝ ክብደት ይጨምራል።”
ተማሪወቹም በመስማማት አንገታቸውን ሲነቀንቁ፣ ቀጠለች፣
“በህይወት ውስጥ ያሉ ጭንቀቶች ልክ እንደዚህ ብርጭቆ ውሃ ናቸው። ለትንሽ ጊዜ ሲይስቡ ምንም ነገር አይከሰትም። ረዘም ያለ ጊዜ ሲያስቡ ትንሽ መታመም ይጀምራሉ። ሀሳብ ዘለግ ላለ ጊዜ ሲቆይ የመድከም እና የመደንዘዝ ስሜት ያስከትላል።