በጣም መጥፎ ጠባይ ያለው አንድ ትንሽ ልጅ ነበር ፡፡ አባቱ አንድ ሻንጣ ሙሉ ምስማር ሊሰጠው ወሰነ። እናም ልጁ በሚቆጣ ጊዜ ከሻንጣው አንድ ምስማር አያወጣ አጥር ላይ እንዲመታ ነገረው፡፡ በመጀመሪያው ቀን ልጁ በአጥር ላይ 37 ምስማሮችን መታ ፡፡ በቀጣዮቹ ጥቂት ሳምንታት ልጁ ቀስ በቀስ ቁጣውን መቆጣጠር የጀመረ ሲሆን በአጥር ላይ እየመታ ያለውን ምስማሮች ቀስበቀስ ቀነሰ፡፡ ልጁ ምስማሮቹን አጥር ላይ ከመምታት ይልቅ ንዴቱን መቆጣጠር ቀላል እንደሆነ ተገነዘበ። በመጨረሻም ፣ ልጁ ሙሉበሙሉ ቁጣውን የሚቆጣጠርበት ቀን መጣ ፡፡ ዜናውን ለአባቱ ነገረው። እንደገና አባቱ ልጁ ቁጣውን በቁጥጥር ስር ባዋለ ቁጥር በየቀኑ ምስማር ከአጥሩ ላይ መንቀል አንዳለበት ነገረው፡፡ በርካታ ቀናቶች አለፉ። እና ወጣቱ ልጅ በመጨረሻም ምስማሮቹ በሙሉ መንቀል መቻሉን ለአባቱ ነገረው፡፡ በመጨረሻም አባት የልጁን እጅ ይዞ ወደ አጥሩ አመራው ፡፡ እንዲህም አለው፦ “ልጄ ጥሩ አድርገሀል ። ግን በአጥሩ ውስጥ ያሉትን ቀዳዳዎች ተመልከት። ከንግዲህ ይህ አጥር እንደድሮው አይሆንም ፡፡ ነገሮችን በቁጣ ሲናገሩ ልክ እንደዚህ ጠባሳ ያስከትላል፡፡ አንድን ሰው በቁጣ ስሜት ገንፍለህ ስታናግር በሰውየው ስሜት ላይ የሚታስከትለውን ጠባሳ፣ ምንም ያክል ጊዜ ሰውየውን ይቅር ብትል ይቅርታ ፈጽሞ ጠባሳውን ሊሽር አይችልም ፡፡"
እና ምን ለማለት ነው
በኋላ ላይ ሊጸጸቱበት የሚችሉትን ንዴትዎን ይቆጣጠሩ። በሚቆጡበት ጊዜ ሰዎችን አይናገሩ ፡፡ በህይወት ውስጥ አንዳንድ ነገሮች መልሰው እድል ሊሰጡ አይችሉምና።