ሰወችን መርዳት ለራስ ነው !

በአንድ ወቅት በአእምሯዊ እና በአካላዊ ጤንነት ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ነበር። በውይይቱ ላይ 200 ተሳታፊወች ታድመው ነበር። በውይይቱ መካከል ተናጋሪው ለእያንዳንዱ ተስታፊ አንድ አንድ ፊኛ ሰጣቸው እና ስማቸውን በላዩ ላይ እንዲጽፉ ነገራቸው። ከዚያም ፊኛዎቹ ተሰብስበው ጠባብ ወደ ሆነ ክፍል ተወሰዱ። ከዚያም ተሳታፊዎች ወደ ትንሿ ክፍል እንዲገቡ ተጠይቀው ስማቸው ያረፈበትን ፊኛ ፈልገው እንዲያገኙ 2 ደቂቃ ተሰጣቸው። ፊኛ የማፈላለግ ተግባር ቀጠለ። ትርምስ ሆነ። ሰዎቹ ፊኛቸውን በቁጭት እየፈለጉ፣ እየተጋፉ እና እየተሯሯጡ ስማቸው ያለበትን ፊኛ ለማግኘት ሞከሩ። ነገር ግን በ2ኛው ደቂቃ መገባደጃ ላይ ስሙ ያለበትን ፊኛ ማንም ማግኘት አልቻለም። ከዚያም ተናጋሪው ተሳታፊዎች ወደ ክፍሉ ተመልሰው በዘፈቀደ አንድ ፊኛ እንዲወስዱ እና ስሙን አይተው ለባለቤቱ እንዲሰጡ ጠየቃቸው። ከዚያም በ 1 ደቂቃ ሁሉም ስሙ ካረፈበት ፊኛ ጋ ተገናኘ።

ተናጋሪው በመቀጠል ለቡድኑ እንዲህ አለ ፡- “ሰዎች በችኮላ የራሳቸውን ህይወት ና ደስታ ለማግኘት ሲፈልጉ እንዲህ ነው። ሰዎች ደስታን ያመጣል ብለው የሚያምኑትን እና የሚፈልጉትን ነገር ለማግኘት ሌሎችን ወደ ጎን ይገፋሉ። ሆኖም፣ የእኛ ደስታ ሌሎች ሰዎችን በመርዳት እና እንደ ማህበረሰብ በጋራ በመስራት ላይ ነው። ሌሎች ሰዎች የራሳቸውን ደስታ እንዲያገኙ ከረዳህ የራስህን ደስታ ታገኛለህ። ደስተኛ መሆን ከፈለግክ ርህራሄን ተለማመድ። ሌሎችን መርዳት ደስተኛ እንድንሆን ያደርገናልና ።

ሌሎችን መርዳት በሦስት መንገዶች ደስታ ያስገኝልናል፡-

1. አቅጣጫ በመቀየር (diversion)፦ የራስዎን ፊኛ ማግኘት ካልቻሉ፣ የሌሎችን ፊኛ መፈለግ ትኩረትዎ እንዲቀየር ያስችልዎታል። ስለራስዎ ጉዳይ ማሰብ ሲቀንሱ ጭንቀቶ ይቀላል። በዚህ ሁኔታ የርህራሄ ስሜት compassion የፍላጎት ስሜትን (need) ይተካል።

2. አተያይ (perspective) :- ራስን በሌሎች ጫማ ላይ አድርጎ የሰወችን ሁኔታ መመልከት perspective ይባላል። ። የጉዳዩ ክብደት ምንም ይሁን ምን ለሌሎች ሰዎች መጨነቅ ሁላችንም በሕይወታችን ውስጥ ተመሳሳይ ችግሮች እያጋጠሙን እንዳለን እንድናስታውስ ይረዳናል ። perspective የሌሎችን እውነተኛ ስቃይ ሲያጋጥመን (ለምሳሌ ሀዘን ወይም ከባድ የአካል ጉዳት) እኛ እነሱ ብንሆን ብለን እንድናስብ ያደርገናል። ለራሳችን ችግሮች እየሰጠን ያለውን ክብደት መገንዘብ ቀላል ነው። ነገር ግን ርኅራኄ(compassion) ማድረግ፣ የራሳችንን ችግሮች በእይታ (perspective) እንድናይ ይረዳናል።

3. ግንኙነት (connection) : ሰወችን በመርዳት ከሌሎች ጋር መገናኘት ደስታን ወደ ህይወቶ ያመጣል። ሰዎች ደስተኛ ለመሆን ከሌሎች ሰዎች ጋር አዎንታዊ ግንኙነት ሊኖራቸው የሚያስፈልጋቸው ማኅበራዊ ፍጡራን ናቸው። ከሌሎች ሰዎች ጋር መገናኘት ህይወታችንን ያበለጽጋል እናም የመርካት ስሜት ይሰጣል።

Post a Comment (0)
Previous Post Next Post