በአንድ ወቅት አንድ በጣም ሀብታም ነጋዴ በከተማ ውስጥ ይኖር ነበር።
አፍቃሪ ቤተሰብ ነበረው እናም ለሕይወት የሚያስፈልጉትን ነገሮች ሁሉ ያዘጋጅ ነበር።
ብዙ ጊዜ፣ ንግዱን ለማስፋፋት እና አዳዲስ ግንኙነቶችን ለማድረግ ሌሎች ሀገሮችን
ለመጎብኘት ከቤት ይወጣ ነበር።
አንድ ጊዜ በረሃ አቋርጦ ወደ ሩቅ ከተማ ለመድረስ ሲል ከቤቱ ማልዶ ጉዞ ጀመረ። በመንገድ
ላይ ለመብላት ጥቂት ውሃ፣ ቴምር እና የደረቁ ፍራፍሬዎችን ይዞ ነበር።
በመንገድ ላይ በረሃ ውስጥ እኩለ ቀን ስለነበረ በጣም ድካም ተሰማው። በአቅራቢያው ያለ የባህር ዳርቻ አይቶ ወደዚያ ሄደ።
እዚያም ፊቱን ታጥቦ ንፁህ ውሃ ያዘ እና ከዘንባባ ዛፍ ጥላ ስር ለማረፍ ተቀመጠ።
የተሸከመውን ቴምር አውጥቶ መብላት ጀመረ።
ቴምር እየበላ እዚህም እዚያ ድንጋይ ይወረውር ነበር። በመጨረሻም ተነስቶ እጁን
ሊታጠብ ወደ ምንጩ ሄደ።
ወዲያው አንድ ኃይለኛ የሚመስል ትልቅ በእጁ የሚያብረቀርቅ ሰይፍ የያዘ ጂኒ ወደ
እሱ ሲሮጥ አየ።
ብዙም ሳይቆይ ጂኒው ከነጋዴው ፊት ቆመ። ጂኒውም "በቅርቡ ልትሞት ነው
አንድዬን ልጄን ለመግደል እንደደፈርክ እገድልሃለሁ!" አለው።
"ምን?! ልጅህን ገድዬዋለሁ?!" አለ ነጋዴው በተንቀጠቀጠ ድምጽ። "አዎ ያ ድንጋዮቹን ስትወረውር የልጄን ጭንቅላት መታውና ሞተ" አለ ጂኒው።
" ይቅርታ ጌታዬ ልጅህን ለመጉዳት ፈልጌ አልነበረም። እባክህ ቸር እና
መሃሪ ሁንልኝ!" ነጋዴው ለመነ።
" ምንም ልመናህን አልሰማም። ልክ እንደ ልጄ ትሞታለህ። አሁን እገድልሃለሁ።"
በእነዚህ ቃላት ጂኒው ነጋዴውን ወደ መሬት አሸማቀቀው። ነጋዴውን ለመምታት እጁን
አነሳ።
ከዚያም ነጋዴው "ጌታ ሆይ የፈለከውን ልታደርግ ትችላለህ ግን እባክህ የመጨረሻ
ምኞቴን አሟላልኝ" አለው።
"እሺ የመጨረሻ ምኞትህ ምንድን ነው?" ጂኒው ጠየቀ ። ነጋዴውም
መለሰ።
"ለመጨረሻ ጊዜ ቤተሰቤን ለማግኘት ወደ ከተማ ልሂድ። ወደ ከተማ ሄጄ እዳዬን
በሙሉ ልክፈል እና ላጽዳ። ለወደፊት ቤተሰቤ ህይወት የሚሆን ገንዘብ አዘጋጅቼ ለድሆች ምጽዋት አደርግ ዘንድ ከሞትኩ በኋላ በገነት
ውስጥ እንድቀመጥ ፍቀድልኝ ።
"ኦህ! ይህ በጣም ብዙ ጊዜ ይወስዳል። እና ለዚህ ምን ያህል ጊዜ ያስፈልግሀል?"
ጂኒው ጠየቀ ።
"ጌታዬ ለዚህ ሁሉ ቢያንስ አንድ አመት ያስፈልገኛል። ልክ ከዛሬ አንድ አመት ቃል እገባለሁ። እዚያው ቦታ ላይ አገኘሀላው። ከዚያም
የልጅህን ሞት ለመበቀል ልትገድለኝ ትችላለህ" አለ ነጋዴው ።
ጂኒው አሰበ። ከዚያም "ከዛሬ ከአስራ ሁለት ወር በኋላ በዚህ ካልሆንክ
እጅግ የከፋ እና ሰቃቂ ሞት ትሞታለህ" አለው።
ነጋዴውም እሺ ብሎ ሰገደ። ከዚያም በፍጥነት ወደ ከተማው ተጓዘ። ለሶስት ቀናት
ያህል ተጓዘ እና በመጨረሻ ቤቱ ደረሰ።
እዚያም ቤተሰቡን አግኝቶ በበረሃ የሆነውን ነገር ነገራቸው። ቤተሰቡ ከእሱ ለመለያየት
ማሰብ አልቻሉም። ምርር ብለው አለቀሱ ነገር ግን ነጋዴው ከአንድ
አመት በኋላ የገባውን ቃል መፈጸም እንዳለበት ተናገረ።
በማግስቱ ነጋዴው በማለዳ ከእንቅልፉ ነቅቶ ብዙም ሳይቆይ የንግድ ጉዳዮቹን በማዘጋጀት ተጠመደ። ጠበቃ አግኝቶ ኑዛዜ አደረገ።
ለሌሎቹ ነጋዴዎች የሚገባውን ሁሉ ሰጠ። ለድሆችና ለችግረኞች ምግብ፣ ልብስና ዲናር
ሰጠ። ከቤተሰቡ ጋር ብዙ ጊዜ አሳለፈ።
ብዙም ሳይቆይ አንድ ዓመት አለፈ። ከዚያም ነጋዴው በበረሃ ከጂኒ ጋር የሚገናኝበት
ቀን መጣ። ሚስቱንና ልጆቹን በእንባ ተሰናበተ። ከዚያም አይኖቹ በእንባ እየተናነቁ ወደ በረሃ ሄደ።
ከዚያም ጂኒውን ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙበት ቦታ ላይ ጠበቀ። በጭንቀት ሲጠብቅ አንድ
ሽማግሌ ወደ እሱ ሲመጣ አየ።
ሽማግሌው ወደ ነጋዴውም መጣና "ሄሎ፣ እዚህ ብቻህን ምን ታደርጋለህ? በእነዚህ
ቦታዎች የሚኖረውን ጂኒ አትፈራም?" አለው።
ነጋዴው አዛውንቱን ሰላምታ ሰጣቸው። ከዚያም አሳዛኝ ታሪኩን ነገረው። አዛውንቱ
ጂኒውን ለማየት ጓጉተው ስለነበር ከነጋዴው ጋር ለመቆየት ወሰነ።
ትንሽ ቆይተው ነጋዴው ሌላ ሽማግሌ ወደ እነርሱ ሲመጣ አየ። እኚህ ሽማግሌ ሁለት
ጥቁር ውሾችን እየመሩ ነበር። ከውሾቹ ጋር ያለው አዛውንት ደረሱና "ሰላም! በዚህ በጠራራ ጸሀይ እዚህ ቦታ እንድትቀመጡ
ያደረጋችሁ ምንድን ነው?" ብለው ጠየቁ።
አዛውንቱ የነጋዴውን አሳዛኝ ታሪክ ተረከላቸው። ከውሾች ጋር የነበረው አዛውንት
ትንሽ አሰበ። ከዚያም "በዚህ ወንድማችን እና በክፉ ጂኒ መካከል ያለውን ግንኙነት ቆየቸ እመለከታለሁ" አለ። ከነጋዴው
ጋር የጂኒውን መምጣት እየተጠባበቁ ተቀመጡ።
ከግማሽ ሰዓት በኋላ አራተኛው አዛውንት ወደ ቦታው መጣ። እሱ ደግሞ ሦስቱ ሽማግሌውች
ምን እየጠበቁ እንደሆነ ጠየቀ። የነጋዴውን እና የጂኒ ሁኔታ ሲሰማ
እሱ ደግሞ የሚሆነውን ለማየት ተቀመጠ።
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ኃይለኛ ነጎድጓድ ሆነ እና ጂኒው ከጭስ ደመና ከፊታቸው
ታየ።
እሳታማ ቀይ አይኖቹ እና በእጁ የያዘው ሰይፍ ነጋዴውን ለመግደል ምን ያህል እንደተናደደ
እና እንደሚጓጓ ያሳያል። ወደ ነጋዴው ሄዶ መሬት ላይ ጣለው።
"አሁን እዚህ ነህ!" ብሎ ጮኸ። "ጊዜህ በመጨረሻ ደርሷል!"
በዚህ ጊዜ ጂኒው የነጋዴውን ጭንቅላት በሰይፍ ለመምታት እጁን ወደ ላይ አነሳ።
ሁሉም አዛውንቶች በፍርሀት እየተንቀጠቀጡ በነጋዴው ዕጣ ፈንታ እያዘኑ ማልቀስ ጀመሩ። ከዚያም ኋላ ያለው
አዛውንት ለጂኒው ንግግር አደረጉ። "ኦ! ጂኒ በኃይልህ ፊት እሰግዳለሁ እባክህ ልመናዬን ስማ።"
ጂኒው በተናደደ ድምፅ “ምን ትፈልጋለህ?” ሲል ጠየቀ። እባካችሁ ታሪኬን አድምጥ። ከነጋዴው የበለጠ ከፉ እያለ
ነጋዲውን አትግደለው።
“ማለት አልገባኝም” አለ ጂኒው።
“ቆይ አንዴ አንድ ታሪክ ላጫውትህ” አሉ አዛውንቱ
ጂኒው ተናደደ ግን የአዛውንቱን ታሪክ ለመስማት ጓጓ። ኋላ ያሉት አዛውንት ታሪካቸውን ነገሩት።