ማታ ማታ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ለመታጠብ የሚሄድ አንድ ሰው ነበረ ።
እናም ከለታት አንድ ቀን መታጠቢያ ቤቱ ውስጥ እንዳለ የመታጠቢያ ቤቱ ጠባቂ ስላላየው በሩን ቆልፎበት ወጣ። እናም ሰውዬው መውጣት ሲፈልግ በሩን መክፈት ስላልቻለ ወደ ውስጥ ተመልሶ ከበሮ መምታት ጀመረ። አንድ ጂኒ ወደ እሱ መጣ ። ሰውየው ከበሮ እየመታ ጂኒው ይጨፍራል።ከዚያ ጂኒው ለሰውየው እንዲህ አለው: - "ከጠየቅከኝ የፈለከውን አደርግልሃለው ምን ላድርግልህ?” ሰውየው እንዲህ አለ ፦ ይህን ከጀርባዬ ያለውን እብጠት እንድታስወግድልኝ እፈልጋለሁ። ጂኒው ከሰውየ ጀርባ ላይ የነበረውን እብጠት አስወገደለት ። እናም ደስተኛ ሆነ።
በዚሁ ሁኔታ ጓደኛውን አገኘው እና መታጠቢያ ውስጥ ሆኖ እያለ ምን እንደተከሰተ አንድባንድ ነገረው። ጀርባው ላይ የነበረው ጉብታ እብጠት በጂኒውን አማካኝነት እንደተወገደለት ነገረው። ጓደኛው እንደዚሁ ለማድረግ ፈልጎ በማለዳ ወደ መታጠቢያ ቤት ሄዶ ከበሮ እየመታ ጂኒውን ጠበቀው። ጂኒው ወደ እሱ መጣና፡- “አንተ ደደብ ሰውየ ምን ከበሮ ትደበድባለህ እዚህ” ብሎ ይደበድበው ጀመር።ከዚያም ሁለተኛው ሰውየ ለመጀመሪያው ሰውየ እንዲህ ብሎ ነገረው፦ “ጂኒው ወደ እኔ መጣ እና ደበደበኝ ፣ ሌላ እብጠት ጨመረልኝ”።